አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
joomla social share plugin
የጎብኘዎች ብዛት
161438
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
134
168
1517

የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

<<እያንዳንዷን ያለችንን ቁራሽ መሬት ሳይቀር ቆጥሮናመዝግቦ በመያዝ ለምንፈልገው ልማት ማዋል የሚያስችለንን አቅም የሚፈጥርልን እና ከሃገር አቀፍ የመሬት መረጃ ስርዓት ጋር በመናበብ ያለንን መሬቶች ለማወቅ የሚያስችለንን ስራ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራል ተቋም ነው፡፡>>የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አሰድ ዚያድ ሃገራችን ኢትዮጵያ ካሉዋት ከፍተኛ ሀብቶች መካከል አንዱ መሬት እና የተፈጥሮ ሃብት መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡ በተለይ መሬት በሃገራችን ለዜጎች ካለው ከፍተኛ ፋይዳ በመነሳት ሕገ መንግስታችን በአንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ (3) ላይ በግልጽ “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡ሃገራችን ኢትዮጵያ ካሉዋት ከፍተኛ ሀብቶች መካከል አንዱ መሬት እና የተፈጥሮ ሃብት መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡በተለይ መሬት በሃገራችን ለዜጎች ካለው ከፍተኛ ፋይዳ በመነሳት ሕገ መንግስታችን በአንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ (3) ላይ በግልጽ “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡


በማለት የደነገገ ከመሆኑም በላይ የከተማ መሬትን ባህርይ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሕገ መንግስቱ ሰነድ ላይ በግልጽ ሰፍሯል፡፡በማለት የደነገገ ከመሆኑም በላይ የከተማ መሬትን ባህርይ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሕገ መንግስቱ ሰነድ ላይ በግልጽ ሰፍሯል፡፡asedz


በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ይህን የመንግስ እና የሕዝብ ሀብት የሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ዋስትና እንዲያረጋግጥ ለማድረግ አስቀድሞ ካዳስተር እና የመሬትና መሬትነክ ንብረምዝገባ ከግምትውስጥያስገባ የመሬትልማት፣ማኔጅመንትእናየአቅም ግንባታማዕቀፍፖሊሲተዘጋጅቶ አገራዊ መግባባት ተፈጥሮበታል፡፡የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ዋስትና እና መረጃ አገልግሎት እምነት የሚጣልበት እንዲሁም እውነተኛ የከተማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት መሰረታዊ መረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት የሚለውን ራዕይ እውን ለማድረግ ኤጀንሲው ትልቅ ስራ ይጠበቅበታል፡፡በዚህ መሠረት የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መረጃ አሰባሰብና አያያዝ ሥርዓት ደረጃውን የጠበቀ፣ የሁሉንም ወገን እምነትን ያተረፈ፣ ፈጣን፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ለተጠቃሚው ቀላልና ውጤታማ ሆኖ፤ በከተማች የኢኮኖሚ ዕድገትና መልካም አስተዳደር ማምጣት በሚያስችል አግባብ በፌደራል እና በእስተዳደሩ ደረጃ በተቀመረ እቅድ ይመራል፡፡በዚህ መሠረት የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መረጃ አሰባሰብና አያያዝ ሥርዓት ደረጃውን የጠበቀ፣ የሁሉንም ወገን እምነትን ያተረፈ፣ ፈጣን፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ለተጠቃሚው ቀላልና ውጤታማ ሆኖ፤ በከተማች የኢኮኖሚ ዕድገትና መልካም አስተዳደር ማምጣት በሚያስችል አግባብ በፌደራል እና በእስተዳደሩ ደረጃ በተቀመረ እቅድ ይመራል፡፡


በመሆኑም መንግስት የተያዙ ይዞታዎችን እንዲሁም የከተማው አስተዳደር ንብረት የሆኑ አገልግሎት ሰጪዎችን እና ክፍት ቦታዎችን በካዳስተር መረጃ ሥርዓት መመዝገብና የመብቶችን ሠነድ መያዝ፣ በየደረጃው መረጃዎችን ወቅታዊ ማድረግና ለተገልጋዩ በተፈለገው የጥራት ደረጃ መረጃዎች መቅረባቸውን በማረጋገጥ፤በከተማችን የመሬትና መሬት ነክ ንብረት የገበያ ልውውጡን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ለከተሞች ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና መልካም አስተዳደር፤ የሚደግፍ የላቀ የመምራትና የመደገፍ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አጠቃላይ ግብ አድርጎ ይሰራል::የሃገራችን ከተሞች ያለፉበት የመሬት አስተዳደሩ ነባራዊ ሁኔታ ዜጎች ማግኘት ያለባቸውን መልካም አስተዳደር እንዳያገኙ አድርጓቸው የቆየ ከመሆኑ አንፃር፤ የህዝብን እምነት ያተረፈ የከተማ መሬት አስተዳደር እንዲፈጠር የዜጎችን የውሳኔ ሰጪነት ያረጋገጠ የይዞታ ማረጋገጥ ሥርዓት አስፈላጊ ነው፡፡የሃገራችን ከተሞች ያለፉበት የመሬት አስተዳደሩ ነባራዊ ሁኔታ ዜጎች ማግኘት ያለባቸውን መልካም አስተዳደር እንዳያገኙ አድርጓቸው የቆየ ከመሆኑ አንፃር፤ የህዝብን እምነት ያተረፈ የከተማ መሬት አስተዳደር እንዲፈጠር የዜጎችን የውሳኔ ሰጪነት ያረጋገጠ የይዞታ ማረጋገጥ ሥርዓት አስፈላጊ ነው፡፡


building1በዚህ ዘርፍ ህጉ በይዞታ ማረጋገጫ ትግበራ፣ በአነስተኛ አስተዳደራዊ እርከን ውስጥ ባሉ የማረጋገጫ መንደር/ብሎክ እና የማረጋገጫ ቀጠና/ ንዑስ ብሎክ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርግ ስለሚደነግግ በሚገነባው የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ከሚያሳድረው እምነት በተጨማሪ የህዝብን ውሳኔ ሰጪነት በማረጋገጥ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን ያሳልጠዋል ::ይህን ተጨባጭ ከማድረግ አንፃር በአነስተኛ አስተዳደር እርከን ውሳኔ ሰጭነትን ከማውረድ በሻገር፣ ህዝብ ሁሉ የሚመክርበትን እድል የሚፈጥር መሰረተ ሰፊ አሳታፊነት ያለው የይዞታ ማረጋገጥ ሂደት ማካሄዱ እንደ


awal ሃገር ባለው የይዞታ ባለመብትነት የመረጃ ክፍተት ያለውን ሥር የሰደደ ችግር የመፍቻ አቅምን በከፍተኛ ደረጃያሻሽላል፡፡ይህ እምነት ሲፈጠር በማንፋክቸሪንግ ኢንዱስተሪው፣ በሪል ስቴት ኮንስትራክሽን፣ በመሰረተ ልማትና በአገልግሎት ሰጪው ዘርፍ የሚሰማራውንም ኢንቬስትመንት ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ተቋማት ደረጃ በሚያሳድረው የመረጃ አስተማማኝነት በጎ ተፅእኖ ምክንያት ዜጎች የቆጠቡት ሃብት በአበዳሪ ገንዘብ ተቋማት አማካኝነት ወደ ኢኮኖሚ ልማቱ እንዲፈስ ያነሳሳል፡፡


በአጠቃላይ በከተማችን የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የተሟላ ሥርዓት ለመፍጠር አይነተኛና ትልቅ ፋይዳ የሚኖረው ይህ ኤጀንሲ በመሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት ላይ የሚደርሱትን የፍትህ መጓደል አስመልክቶ ለዜጎች ትልቅ አፈይታ የሚሰጥ እና ከመሬትና መሬት ነክ ንብረት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መብቶች፣ ክልከላዎች እና ግዴታዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ወቅታዊ፣ ፈጣን፣ የገበያ ልውውጥ ጋር የተጣጣመ የህግ ማዕቀፍ በማውጣት መሬትና መሬት ነክ ንብረት በነፃ የኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታ ላይ አስተዋጽኦ እንዲኖረው በማድረግ ማንኛውም ዜጋ በመሬት ላይ ላፈራው መሬት ነክ ንብረት የህግ ዋሰትና በመስጠት ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና አካባቢያዊ ልማት ለማፋጠን ትልቅ ሚና የሚጫወት ተቋም ነው፡፡የመሬትናመሬትነክንብረትምዝገባናመረጃሥርዓት በአብዛኞቹ የአገራችን ከተሞች ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ&አጠቃቀምና አስተዳደር ስርአት የሌለ መሆኑን በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡


የአዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች የተሟላ የመሬትና መሬት ነክ መረጃ አለመኖር የመኖሪያ ቤቶችን&የመሰረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመገንባት የሚያስችል ተስማሚ የሆነ ክፍት ቦታ ለመለየት በአገልግሎት ላይ ያሉትንም በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ አውቆ ለመስጠት የንብረት ባለቤትነት ዋስትና ለማረጋገጥ እና የከተሞችን ገቢ ለማሳደግ የተያዙ ጥረቶችን አንቆ ይዟል፡፡ building2


ከዚህ በተጨማሪ በመሬት ዘርፍ ላይ ያሉ የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎች በዘመናዊ አሰራርና ቴክኖሎጂ ሳይደገፉ የተዘገጁ ወጥነት የሌላችው እርስ በርሳቸው የማይናበቡና በቀላሉ ለመዛባት የተጋለጡ ከከተሞች ዕድገት ጋር የመጡ ለውጦችን አካቶ መሄድ በሚያስችል መልኩ ያልተደራጁና መረጃዎችን ወቅታዊ ለማድረግ ያላስቻሉ ሲሆኑ በዘርፉ የነበሩ የአደረጃጀትና አሰራር ችግሮች ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር በመዳመር የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዳይቻል አድርገዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ሥርዓት ዝርጋታው ደረጃ ወጥቶለት እና ተገቢዉ እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ተይዞበት እየተፈፀመ ባለመሆኑ አብዛኛዎቹም አሰራሮች ግልፅ ዓላማ ኖሯቸው የተጀመሩና መረጃን ተከታትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስችሉ ባለመሆናቸው፤ እንዲሁም በህግ ፊት እንደማስረጃነት እንዳያገለግሉ ሕጋዊ ማዕቀፍ የሌላቸው በመሆናቸው ጥረቶቹ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡በመሆኑም እስካሁን ከተከናወኑት የካዳስተር ሥራዎች ጋር በተያያዘ የታዩት ዋና ዋና ችግሮች መካከል የንብረት ዋስትናን ማረጋገጥ አለመቻል፣ ቀልጣፋ የንብረት ገበያ አለመፍጠር፣ የከተሞችን ገቢ አለማሻሻል፣ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ ለእነዚህ ችግሮች በአፋጣኝ መፍትሄ ባለመሰጠቱም በግለሰብ ደረጃ ንብረትን ወደ ገበያው ለማስገባት አለመቻልና ልውውጦችን ከአስተዳደሩ ዕውቅና ውጪ በማድረግ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳያገኝ አድርጓል፡፡


የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ የመሬት ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ፣ መብትን ለሌወገንማስተላለፍታክስ ከመሰብሰብ፣የይዞታን ትክክለኛነት ማረጋገጥ መሳሰሉት አላማዎች አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ቢሆንም፤ በበርካታ ከተሞች ይህንን የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ለማከናወን አግባብ ያለውና ግልፅ የሆነ አሠራር ሳይዘረጋ በመቆየቱ በህገ-ወጥ መንገድ መሬት የመያዝና ይህንኑም በከፍተኛ ዋጋ ሸጥ ሁኔታ ተበራክቶ ቆይቷልህን ሁኔታ ለማሻሻል የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ሥርዓት ኘሮጀክት ለመነሻነት በአዲስ አበባ ተቀርጾ የተግባራ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ ግቦች የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ሥርዓት ተዘጋጅቶለት በከተሞች በሥራ ላይ እንዲውል፣ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫና ግብይት እንዲሁም የመሬት አስተዳደር ሥራ በትክክለኛ መረጃና አሠራር የተደገፈ እንዲሆን በአዲስ አበባ የሕጋዊ ካዳሰተር መረጃ የማደራጀት ስራ ቀድሞ በማከናወበመቀጠልም ተሞክሮ በመቀመር የክልል ከተሞችን ህጋዊ ካዳስተር የማደረጀት አቅጣጫ ተይዞ ወደ ፕሮግራሙ ተገብቷል፡፡በመሆኑም መንግስት የመሬትና መሬት ነክ መረጃ በተሟላ መልክ መኖር የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሂደቱን ይበልጥ የተሳለጠና ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስችል ተረድቷል፡፡