አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
joomla social share plugin
የጎብኘዎች ብዛት
131922
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
59
190
477

የቢሮ ሀላፊ መልዕክት

derara

በአገራችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት በማይናወጥ መሠረት ላይ ከተጣለ ወዲህ የወቅቱ ትውልድ መሰረታዊ አጀንዳ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መሠረተ ልማቶች መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአስተዳደራችን ይህንን አንገብጋቢ ጥያቄ ለመመለስ ወሳኝ ተልእኮ ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አንዱ ነው፡፡መስሪያ ቤታችንም ራሱን ችሎ ከተቋቋመ ጀምሮ ይህንን ታላቅ አደራ ተረክቦ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ተልእኮውንም ለመፈፀም የሚያስችል መዋቅርና አደረጃጀት በመፍጠር ቀልጣፋና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በማስፈን ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ላይ መሆናችን ለቀጣይ ስራችን አቅም ፈጥሮልናል፡፡ ሌላው የመሬት እና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ እና መረጃን፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታና ገበያ አገልግሎት፣ የመሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ፣ የከተማ ፕላንና መረጃ ዝግጅት፣ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ስራዎች በዋናነት ለቢሯችን ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

«StartPrevNextEnd»