አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
የጎብኘዎች ብዛት
161426
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
122
168
1505

ተግባርና ኃላፊነት

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የድሬዳዋ ከተማ መሬትን ለማልትና ለማስተዳደር በድሬዳዋ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 21/2004 አንቀጽ 32 መሰረት የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰተዉታል

ይህ ቢሮ ተጠሪነቱ ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆኖ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፣

  1. የመሬት እና መሬትነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ”፣ የመሬት ግብይትና የይዞታ አስተዳደር፣የመሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ የከተማ ፕላንና መረጃ ዝግጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ስራዎችን ይፈጽማል ይመራል፣
  2. ሴክተሩን በሚመለከት የወጡ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፣
  3. ሴክተሩን በተመለከተ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ ሃሳቦችን ያመለጫል፣ ለሚመለከተዉ አካል በማቅረብም ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣
  4. ስለአስተዳደሩ ቦታዎች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች አመዘጋገብና መረጃ አያያዝ የወጡ ፖሊሲዎና ህጎች ተፈጻሚ ያደርጋል፣ ከህግ ዉጪ በሚሰሩ የቦታ መስተላለፎች/ መረጃ አያየዘዞች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ያስወስዳል፣
  5. ከተማዋ በፕላን እንድትመራ የከተማዉ የመሬት አጠቃቀምና ግንባታ አፈጻጸም የወጡ ፕላኖችን የተከተሉ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስርአት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርገል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
  6. ከተማዋ በፕላን እንድትመራ የከተማዉ የመሬት አጠቃቀም ግንባታ አፈጻጸም የወጡ ፕላኖችን የተከተሉ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስርአት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ይደረጋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
  7. በከተማዋ የመሬት አቅርቦቱና ፍላጎቱ ሚዛኑን ጠብቆ መሄድ እንዲችል የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን የመፍትሄ እርምጃዎችን ይወስዳል፣
  8. የመሬት ልማትና ማኔጅመንት አፈጻጸምና መሬት ለተጠቃሚዎች የሚፈቀድባቸዉ ሥርዓቶች የሚመሩባቸዉን የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያዎች በጥናት ወቅታዊ ያደርጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ተግባራዊነታቸዉን ይከታተላል
  9. የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማዕከል ያደረገ የመሬትና የከተማ ልማት የሚያስችል የህብረተሰብ ተሳትፎ በየአካባቢለዉ እንዲደራጅ ድጋፍ ያደርጋል፣
  10.  የፕላን ማጣጣም ማሻሻል ስራዎችን ያከናዉናል፣
«StartPrevNextEnd»