አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
የጎብኘዎች ብዛት
161434
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
130
168
1513

የተቀናጀ መሬትና መሬት ነክ መረጃ ስርዓት ዝርጋታ

ተልዕኮ

በድሬዳዋ ከተማ የመሬት መረጃ አያያዝ እና አሰጣጥ ስርዓት በሀገሪቱ የመሬት ፖሊሲና ስትራቴጂ በመመራት የከተማዋን የመሬትና መሬት ነክ መረጃ በተቀናጀ እንዲሁም በዘመናዊ መልኩ በማዘጋጀትና በመከለስ ቀልጣፋና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የመሬት አስተዳደር ስርዓት መፍጠር ነው፡፡

ራዕይ

በ2011 ዓ.ም የድሬዳዋ ከተማን የመሬት መረጃ አያያዝ እና አሰጣጥ ስርዓቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ሆኖ ማየት፡፡

 

የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የሚከናወኑ ተግባራት

 •         የከተማዋን የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች የመዘርጋትና የማስፋፋት ሥራ ያከናውናል፣
 • የከተማዋን መሠረታዊና የካዳስተር ካርታ ያዘጋጃል፡፡
 • በከተማዋ ሠርቬይ በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ የካዳስተር ዲጂታል ካርታ ያዘጋጃል
 • በከተማዋ ደረጃውን የጠበቀ የአድራሻ ሥርዓት በመተግበር የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል፣
 • የቤት ለቤት መረጃን በመሰብሰብ ፣የነባር የይዞታ ሠነድ መረጃዎችን ወደ ዲጂታል በመቀየር ህጋዊ የካዳስተር መረጃውን እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡
 • ለሥርዓቱ ዝርጋታ አስፈላጊ የሆኑ የቅየሳ መሣሪያ፣ የሀርድዌርና የሶፍትዌር የማልማት እና ግዥ እንዲከናወን ያደርጋል
 • በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል የሰው ሀይል ልማት ፕሮግራም ፕሮጀክት ይቀርጻል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣
 • የተለያየ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ለመተንተን የሚያገለግል የሲስተም ጥናት ያካሂዳል፣ ተግባራዊም ያደርጋል
 • የቤት ለቤት መረጃን በመሰብሰብ፣ የነባር የይዞታ ሠነድ መረጃዎችን ወደ ዲጂታል በመቀየር ህጋዊ የካዳስተር መረጃውን እንዲጠናከር ያደርጋል፣
 • የተቀናጀ እና በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት የተደገፈ የመሬት መረጃ ለተገልጋይ እና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ያደርጋል፡፡
 • አላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል