አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
የጎብኘዎች ብዛት
140415
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
43
182
1038

የሽንሻኖ ማስተካከል

ዋና ዋና ተግባራት

 •              የመሬት ሽንሻኖ ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን ጥናት ከከተማ ፕላን እና መረጃ ዝግጅት አብይ የስራ ሂደት አስቀድሞ መረከብ ይኖርበታል፡፡ ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን ጥናት የሌለው ከሆነ አስቀድሞ እንዲጠናለት ለከተማ ፕላን እና መረጃ ዝግጅት አብይ የስራ ሂደት ማቅረብና ማስጠናት 
 •         በሽንሻኖና ቅየሳ ተግባር የሚሳተፉ ለሙያው አግባብ ያላቸው ባለሙያዎች በመምረጥ /በመቅጠር/ መመደብ ይኖርበታል
 •        ለሽንሻኖና ቅየሳ ባለሙያዎች ስለከተማ ፕላን ህግጋት፤ስለአጠቃላይ የሽንሻኖ ጥናት አሰራርና የትግበራ ዘዴዎች እንዲሁም በሽንሻኖ መሳሪያዎች አጠቃቀም ዙሪያ በስራው ላይ ለሚገኙና ወደ ስራ ለሚገቡ ሰራተኞች ልምድ ባላቸው ተቋማት ወይም በዘርፉ በተሰማሩ አማካሪዎች ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል
 •          በካርታላይየሚፈፀሙትንሽንሻኖዎችየቴክኒክቡድንበማዋቀር በየጊዜውበመገምገምየጥራትቁጥጥርማካሄድይኖርበታል
 •          የተዘጋጁ ሽንሻኖዎች አግባብ ባለው አካል እንዲጸድቁ በማድረግ በከተማው መረጃ ማዕከል በቤዝ ማፕ ላይ እንዲካተት ማድረግ አለበት፣
 •         የመስክ የልኬትና የቅየሳ ስራዎችን ለመፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማካሄድ አለበት
 •     ተዘጋጅተው የቀረቡ ፕላኖች ከነባራዊ ሁኔታው ጋር ተጣጥመው የተዘጋጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ከተማው መዋቅራዊ ፕላን የተዘጋጀበትን የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች (Ground Control Points/GCP) በሚገባ መቀመጡና ለስራው የማያስቸግር መሆኑን ማረጋገጥ
  •          ወደ መስክ ከመወጣቱ በፊት ዝርዝር የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች X,Y Co-ordinate ወደ ቶታል ስቴሽን Upload አድርጎ ማዘጋጀት፣
  •      መስክ ተወጥቶ የሚታዩ ልዩነቶችን ለመልቀም በሚያስችል መልኩ የአካባቢዉን ዝርዝር ሽንሸና ለስራ በሚያመች Scale ሃርድ ኮፒ ማዘጋጀት
«StartPrevNextEnd»