አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
የጎብኘዎች ብዛት
161427
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
123
168
1506

የአሰራር ጥራት ኦዲት፣ አቤቱታና ቅሬታና አፈታት

ራዕይ

በቢሮው የሚሰጡ አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ እንዲሆኑ በማድረግ የተገልጋዩን እና የባለድርሻ አካላትን አመኔታ በመጨመር በመሬት ልማትና ማኔጅመንት በኩል ያሉ ችግሮችን ተፈተው ማየት፡፡

 

ተልዕኮ

በቢሮው የሚሰጡ አገልግሎቶች በወጣው እስታንዳርድና መመሪያ መሰረት ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ የህብረተሰቡን ቅሬታና አቤቱታ ተቀብሎ ፈጣን እና ዘለቄታዊ ምላሽ በመስጠት መልካም አስተዳደር ማስፈን፡፡

 

ስልጣን እና ተግባራት

  • የአሰራር ጥራት ኦዲት ስልት ይነድፋል በሚመለከተው አካል ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • የአሰራር ጥራት ኦዲት ለማከናወን የሚረዱ መረጃ ያሰባስባል ያጣራል
  • የአሰራር ጥራት ኦዲት ያከናውናል
  • የአሰራር ጥራት ኦዲት ሪፖርት ያዘጋጃል
  • በሪፖርቱ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል /ያስወስዳል/
  • የነዋሪዎችን ቅሬታና አቤቱታ ይቀበላል ይመዘግባል
  • የነዋሪዎቹን ቅሬታና አቤቱታ ይመረምራል ፣ያጣራል
  • የቅሬታና አቤቱታ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል ፣ያስወስናል /ይወስናል/