አዲስ ጉዳይ
ማህበራዊ ድህረ-ገፆች
የጎብኘዎች ብዛት
161432
ዛሬ
የትናንት
በዚህ ሣምንት
128
168
1511

የስርዓተ ፆታና ኤች አይ ቪ

ራዕይ

ራሱንና ቤተሰቡን ከኤች አይቪ /ኤድስ የጠበቀና የሴቶችን ተሳትፎ እኩል ተጠቃሚና ተደራሽ ያደረገን ሰራተኛ ተፈጥሮ ማየት.

 

ዋና ዋና ተግባራት

 • የኤች አይ ቪ ኤድስ እና የስርአተ ጾታ ስርጸት ፕሮግራም የግንዛቤ ማስጨበጫ ማዘጋጀት
 • ለኤች አይ ቪ ኤድስ ሜይንስትሪሚንግ የተመደበ በጀትን መጠን በተመለከተ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የበጀት አመዳደብን መቃኘት.
 • የኤች አይ ቪ ኤድስ በቢሮ ሰራተኞች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽእኖ ከመቀነስ እና ከመቋቋም እንጻር ለተሰጡ ምላሾች የዳሰሳ ጥናት ማድረግ.
 • ወላጆቻቸውን በኤድስ ላጡ ልጆች ድጋፍና ምክር አገልግሎት መስጠት.
 • በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱ (ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ) ጋር ግንኙነት መፍጠር.
 • ለሰራተኛው የምክርና እና የደም ምርመራ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ.
 • የኤች አይ ቪ ኤድስ እና የስርአተ ጾታ በመደበኛ እቅድ አካቶ በመተግበር ረገድ የክትትልና ግምገማ ስርአት መዘርጋት.
 • በስራ ቦታ ላይ በጾታ ምክንያት ለሚያጋጥሙ ችግሮች ለሴት ሰራተኞች የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት
 • በቢሮ የስራ አፈጻጸም የስርአተ ጾታ እኩልነት መረጋገጡን መከታተል
 • በመስክ በመገኘት በሴቶች ዙሪያ የተከናወኑትን ስራዎች መከታተል.
 • የትምህርት የስልጠና እድሎች የምልመላና መረጣ ስራዎችን ፍትሀዊነት መከታተል.